የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው።

44

ደሴ: ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ወሎ ዞን፣ የሰሜን ወሎ ዞን፣ የደሴ፣ የኮምቦልቻ እና የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ መሪዎች በቀጣናው ሰላም እና ፀጥታ ዙሪያ እየመከሩ ነው። በመድረኩ በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ እና በቀጣይ የትኩረት መስኮች እየተወያዩ ነው።

በውይይቱ ላይ ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የሰሜን ምሥራቅ እዝ ዋና አዛዣ ጄኔራል አሰፋ ቸኮል፣ በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር)፣ የዞን አስተዳዳሪዎች፣ ከንቲባዎች እና የሰላም እና ፀጥታ ሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፡- ከድር አሊ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ባለሃብቶችን ለመሳብ ምቹ ኹኔታዎች እንፈጥራለን” የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ
Next articleርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሀ ግብርን በማስመልከት ያስተላለፉት መልእክት፦