
ባሕር ዳር: ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በአቅርቦት እጥረት ምክንያት ለመጪው በዓል በሚውሉ ምርቶች ላይ የዋጋ መናር እንዳይፈጠር በቂ ዝግጅት መደረጉን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ.ር) ተናገሩ። ከ115 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ጅቡቲ መድረሱን የገለጹት ሚኒስትሩ በቀናት ውስጥ ወደ ምርት ማዕከል እንደሚገቡም ነው የጠቆሙት፡፡
አክለውም ሌሎች መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች ወደ ምርት ማዕከል እንደሚገቡም ጠቅሰዋል፡፡
ከሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ እንደተገኘው መረጃ ዝቅተኛው የማኀበረሰብ ክፍል እንዳይጎዳ መንግሥት በጥንቃቄ እየሠራ መኾኑን ያነሱት ሚኒስትሩ ሥራው ውጤታማነት እያሳየ መኾኑን ገልጸዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
