
ባሕር ዳር: ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ፀሐይ ወይብላ ቅድስት ማርያም ካቴድራል እየተከበረ በሚገኘው በዓል ላይ የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ በርናባስ፣ የዋግ ኽምራ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አሥኪያጅ ሊቀ ህሩያን ኃይሌ ዓለሙ፣ የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ ኃይሉ ግርማይ፣ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኀላፊ ከፍያለው ደባሽ፣ የደብር አሥተዳዳሪዎች፣ የሃይማኖቱ ተከታዮች እና የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን ተገኝተዋል፡፡
በበዓሉ ላይ የሃይማኖት አባቶች ወረብ፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን መዝሙር፣ ሃይማኖታዊ ይዘቱን የጠበቀ ትምህርት እና የሻደይ በዓልን የተመለከቱ አስተምህሮዎች ይቀርባሉ ተብሎም ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡- ደጀን ታምሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
