
ባሕር ዳር: ነሐሴ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 20 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እንደገለጹት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ተቋሙ 19 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት አቅዶ 20 ቢሊየን ብር አግኝቷል።
ለውጭ ሀገራት ከተደረገ የኃይል ሽያጭም 140 ሚሊየን ዶላር መገኘቱን ገልጸው ይኽም ከባለፈዉ ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ16 በመቶ ጭማሪ እንዳለዉ ተናግረዋል።
በ2016 ዓ.ም 20 ሺህ 522 ጊጋ ዋት በሰዓት ኃይል ማምረት መቻሉን የገለጹት ዋና ሥራ አስፈጻሚው በዚኽም የዕቅዱን 98 በመቶ ማሳካት መቻሉን ጠቁመዋል። የሀገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍጆታ በ17 በመቶ ከፍ ማለቱም ተጠቁሟል።
ከኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማኀበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በቀጣይ በጀት ዓመት 263 ሚሊየን ዶላር ለማግኘት ታቅዶል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
