የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ልጇን በግፍ ለተነጠቀቸው የሕጻን ሄቨን እናት የመኖሪያ ቤት አበረከተ።

49

ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ልጇን በግፍ ለተነጠቀችው ሕጻን ሄቨን እናት የመንግሥት መኖሪያ ቤት አበርክቷል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አሥተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ የሄቨንን እናት በማግኘት አጽናንተዋል::

ልጇን በግፍ ተነጥቃ ባለፈው አንድ ዓመት ፍትሕ ሳታገኝ ለቆየችው ሲስተር አበቅየለሽ የፍትሕ ሒደቱን ለመከታተል ፣ያለችበት ሁኔታ የተሻለ እንዲሆንላትና ተጋላጭነቷን ለመቀነስ እንዲመች የከተማ አሥተዳደሩ አንድ የመንግሥት መኖሪያ ቤት አበርክቷል፡፡ ከዚህ ባለፈም በሙያዋ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እንድትሠራ መመቻቸቱን ነው ከንቲባ አዳነች የገለጹት፡፡

የህጻን ሄቨን ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ በመሆኑ ድርጊቱ ተገቢውን ፍትሕ ማግኘቱ የሌሎች ህፃናት ተጋላጭነትን ለመቀነስ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን ከንቲባዋ አስገንዝበዋል፡፡ መሰል ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት እንዳይፈፀም የማኅበረሰቡ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ እና ችግሩ የጋራ ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም ኀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከመጭው መስከረም 7/2017 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ትምህርት ይጀመራል” የማዕከላዊ ጎንደር ዞን
Next article“ወልድያን ሊቀይሩ የሚችሉ የልማት ሥራዎች በጥሩ ኹኔታ ቀጥለዋል” የወልድያ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዱባለ አብራር