20

“ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ የኅብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሰው ተኮር የልማት ሥራዎች አጠናክሮ መሥራት ይገባል” ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር)

ባሕር ዳር: ነሐሴ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በደሴ ከተማ አሥተዳደር “ውጤታማና ቀልጣፋ አገልግሎት ለሀገር ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ የ2016ዓ.ም የማጠቃለያ ግምገማና የ2017ዓ.ም የዕቅድ ትዉዉቅ መድረክ ከከተማ የመንግሥት ሠራተኞች ጋር አካሂዷል።

የመንግሥትና የፓርቲ ተግባራትን በይቻላል መንፈስ እና በቁርጠኝነት ከተመራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤት ማየት እንደምንችል በየመዋቅሩ ያሉ ለውጦች ማሳያ መኾናቸውን የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር) ገልጸዋል።

የተጀመሩ ተጨባጭ የልማት ሥራዎችን በማከናወን የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሰፊ ርብርብ ማድረግ እንደሚጠበቅም ዶክተር ዘሪሁን መናገራቸውን ከክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በቀጣይም ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ የኅብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሰው ተኮር የልማት ሥራዎች አጠናክሮ መሥራት ይገባል ነው ያሉት። ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ ተቀጣጥሎ የተጀመረውን ሥራ ከዳር ማድረስ ይገባል ብለዋል።

የ2016ዓ.ም ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2017ዓ.ም እቅድ የደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ አዝመራ ማስረሻ አቅርበዉ ወይይት ተደርጓል።

በመድረኩም የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር)፣
የአማራ ክልል ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሀናን አብዱ፣ የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ሳሙኤል ሞላልኝ፣ የደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አሸናፊ አለማየሁ፣ በብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የወጣቶች ሊግ ኀላፊ ወጣት ተስፋሁን ተሰማን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የመንግሥት ሠራተኞች ተገኝተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
👇ቀጣዮችን ማስፈንጠሪያዎች በመጫን የአሚኮ ቤተሰብ ይሁኑ
ድረገጽ www.ameco.et
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
ረምብል https://rumble.com/c/c-4646842
ቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ኤክስ (ትዊተር) https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ኢንስታግራም https://instagram.com/ameco.et
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://bit.ly/48iEHRC
አሚኮ ስፖርት https://bit.ly/3rkHxVF
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ http://bit.ly/469N8wG

Previous articleየማኅበራዊ ሚዲያ አውታሮችን እንዴት እንጠቀም?
Next article“የክልሉ የአገልግሎት ዘርፍ ፍኖተ ዕቅድ ሰብዓዊ ካፒታልን መገንባት ዓላማ ያለው ነው” የኢኮኖሚ አማካሪው ሰኢድ ኑሩ (ዶ.ር)