የሻደይ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ፖሊስ አስታወቀ።

28

ባሕር ዳር: ነሐሴ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ በየዓመቱ በድምቀት የሚከበረውን የሻደይ በዓል በሰላም ለማጠናቀቅ ዝግጅት መደረጉን ፖሊስ አስታውቋል።

የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ደጀን ወዳጅ ከብሔረሰብ አሥተዳደሩ እስከ ወረዳ የቅድመ ዝግጅት ሥራው ተጠናቅቆ ወደ ተግባር እንደተገባ ገልጸዋል።

በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲያልፍ ከአጋር የፀጥታ አካላት ጋር እየተሠራ መኾኑን እና የሚፈጠሩ ችግሮች ካሉም አደረጃጀት ተዋቅሮ ሥራውን ለመሥራት ዝግጅት እየተደረገ መኾኑን ነው ያስገነዘቡት።

በዓሉ በዞኑ በሚገኙ ቦታዎች ሁሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ወንጀልን ከመከላከል አስከ ትራፊክ ፍሰቱ የተሳለጠ ለማድረግ ከሁሉም ወረዳዎች ጋር ውይይት ተደርጎ ወደ ተግባር መገባቱን ነው የተናገሩት።

በዓሉ ተጀምሮ እስከ ሚጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ እና ከፀጥታ መዋቅሩ ጎን እንዲኾን መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሌተናል ጀኔራል የመታሰቢያ ሙዝየም የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።
Next articleበዞኑ ለሚያለሙ ባለሃብቶች ምቹ እና ቀልጣፋ አሠራር እንደሚፈጥር የሰሜን ወሎ ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ አስታወቀ።