
ባሕር ዳር: ነሐሴ 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡ በመድረኩ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር) የመንግሥት ሠራተኛውን በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ግንዛቤ በማስጨበጥ ለሰላም የራሱን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ማድረግ የመድረኩ ቀዳሚ ዓላማ መኾኑን ገልጸዋል፡፡
ዶክተር ዘሪሁን የመንግሥት ሠራተኛው የአገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን የኅብረተሰቡን ችግር መፍታት ላይ በትኩረት መሥራት ይገባዋል ብለዋል።
የመንግሥት ሠራተኞቹ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን በማስቀጠል በ2017 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም እንዲኖራቸው ማድረግ ላይም ውይይት ማድረጋቸው ነው የተገለጸው፡፡
ዘጋቢ:- አበሻ አንለይ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!