የሻደይ በአልን ምክንያት በማድረግ በሰቆጣ ከተማ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።

30

ሰቆጣ: ነሐሴ 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሰቆጣ ከተማ የሻደይ በአልን ምክንያት በማድረግ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።

በመርሐ ግብሩም የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ዋና አስተዳዳሪ ኃይሉ ግርማይን ጨምሮ ከፍተኛ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ መሪዎች ፣ የየወረዳ የባሕልና ቱሪዝም መሪዎች፣ የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር ሴት መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ነው።

የፓናል ውይይቱ በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ሴቶች ህጻናትና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ የተዘጋጀ ሲኾን
“ሻደይ ባሕላችን ለሰላማችንና ለዘላቂ አንድነታችን” በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው። በፖናል ውይይቱ ላይ “ሻደይና የሴቶች ነጻነት” በሚል ርዕሰ ጥናታዊ ጽሑፍ ይቀርባል።

በውይይት መድረኩ “የሻደይ በዓል ለሀገራዊ የሰላም እሴት ግንባታ ያለው አስተዋጽኦ” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የፓናል ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ዘጋቢ:- ደጀን ታምሩ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኮምቦልቻ ከተማን የውኃ ችግር ይፈታል የተባለው ፕሮጀክት!
Next articleየአውሮፓ ኅብርት እና ዩኒሴፍ የሕክምና መሳሪያዎች እና መድኃኒቶችን ለአምስት ክልሎች ድጋፍ ማድረጋቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡