
ባሕር ዳር: ነሐሴ 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ)👉 ራሂም ስተርሊንግ ጁቬንቱስን ሊቀላቀል እንደሚችል ተሰምቷል። እንደ ሜል መረጃ ስተርሊንግ በቼልሲ ቤት ቆይታው አልተረጋገጠም።
👉 ወልቭስ የአርሰናሉን ግብ ጠባቂ አሮን ራምስዴልን በውሰት ለማስፈረም እየሠራ ነው። በአትሌቲክ መረጃ መሰረት ወልቭስ ራምስዴልን በውሰት ማስፈረም እና በቀጣይ ዓመት ደግሞ በቋሚነት ማዛወር ነው የፈለገው።
👉 ፉልሃም ስኮት ማክቶሚኒን ከዩናይትድ ለማስፈረም ጥረት ላይ ነው። ቲም ቶክ እንዳስነበበው ፋልሃም ለማክቶሚኒ ዝውውር ለዩናይትድ ሁለት ጥያቄ አቅርቦ ውድቅ ተደርጎበታል።
👉 ኒውካስትል ማርክ ጉሂን ከፓላስ ለማስፈረም የሚያደርገውን ጥረት ቀጥሏል። በአማራጭነት የሊቨርፑሉን ጆ ጎሜዝን እና የቼልሲው ቻላባህ ለማግኘት እያሰበ ስለመኾኑ ያስነበበው አይ ስፖርት ነው።
👉 ቼልሲ ለሮሚዮ ሉካኩ ዝውውር 34 ሚሊዮን ፓውንድ ይፈልጋል፤ እንደ ቢቢሲ መረጃ ናፖሊ የሉካኩ ፈላጊ ሲኾን ቼልሲ ሉካኩን በቋሚነት እንጂ በውሰት ለመስጠት ፈቃደኛ አይደለም።
👉 ጋርዲያን ደግሞ ማንቸስተር ዩናይትድ ኡጋርቴን ለማግኘት እስከ ዝውውር መስኮቱ መጨረሻ ድረስ እንደሚሠራ ጽፏል። ድርድሩ ካልተሳካም በውሰት ተጫዋቹን ለማግኘት ማቀዱም ተሰምቷል።
👉 የሳኡዲው አል ሂላል ከማንቸስተር ሲቲ ካይል ዎከር እና ጃኦ ካንሴሎን የማስፈረም ፍላጎት እንዳለው የጋርዲያን መረጃ ያሳያል።
👉 ማንቸስተር ሲቲ ኢልካይ ጉንዱጋንን ከባርሴሎና መልሶ ለማስፈረም ፍላጎት አሳይቷል። በአትሌቲክ መረጃ መሰረት ጀርመናዊዉ ጉንዱጋን ከባርሴሎና እንዲወጣ የስፔኑ ክለብ ፍላጎት ነው።
👉 ሪያል ሶሴዳድ ማይክል ሚሪኖን ለማስፈረም አርሰናል ያቀረበውን ገንዘብ አልተቀበለም። ተጫዋቹ አርሰናልን ለመቀላቀል እንደሚፈልግ ሚረር አስነብቧል።
👉 ብሬንት ፎርድ አጥቂው ኢቫን ቶኒን ለሳኡዲው አል ሃሊ ለመሸጥ አቅዷል። ታይምስ እንደሚለው የእንግሊዙ ክለብ ከተጫዋቹ ዝውውር 50 ሚ ፓውንድ ይፈልጋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!