ጃኦ ፊሊክስ ቼልሲን ለመቀላቀል ተስማማ።

26

ባሕር ዳር: ነሐሴ 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአትሌቲኮ ማድሪዱ ፊሊክስ ቼልሲን ለመቀላቀል ለንደን ደርሷል። ተጫዋቹ ባለፉት ዓመታት በውሰት በቼልሲ እና ባርሴሎና አሳልፏል። አሁን ደግሞ በቋሚነት ቼልሲን ለመቀላቀል ተቃርቧል።

ፖርቱጋላዊ አጥቂ በእንግሊዙ ክለብ ለስድስት ዓመታት የሚፈርም ሲኾን እንደ አስፈላጊነቱ የሚጨመር የአንድ ዓመት ጭማሪም ዉሉ ላይ እንደሚገኝ ስካይ ስፖርትስ አስነብቧል።

የፊሊክስን ወደ ቼልሲ መጓዝ ተከትሎ በቼልሲ እና አትሌቲኮ ማድሪድ መካከል በኮነር ጋላገር ዝውውር ዙሪያ ተቋርጦ የነበረው ድርድር ተስፋ ማገኘቱም ታውቋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article1 ነጥብ 4 ሚሊዮን የሚገመቱ የፀረ ወባ መድኃኒቶች ሊሠራጩ መኾኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
Next articleአጫጭር የስፖርት ዜናዎች