
ባሕር ዳር: ነሐሴ 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮ ቴሌኮም ከቪዛ ኩባንያ ጋር በመተባበር በኢትዮዽያ የመጀመሪያውን በኪስ የሚያዝ ‘ቨርቱዋል ቪዛ’ ካርድ ብሎም የተሻሻለ የሀዋላ አገልግሎት በቪዛ ዳይሬክት እና በቴሌብር ረሚት አቅርቧል።
ይህንን አስመልክቶም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልእክት “በዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ አንድ እመርታ የታየበት ደረጃ ላይ ደርሰናል” ብለዋል።
ቪዛ ዳይሬክት ከ190 ሀገራት በላይ ቀለል ያለ የገንዘብ ማዘዋወር አገልግሎትን በቴሌብር ቨርቱዋል ካርድ ቁጥር አማካኝነት የሚያቀላጥፍ ይኾናል።
ይህ አዲስ አገልግሎት ከ47 ነጥብ 55 ሚሊዮን በላይ የኾኑ የቴሌብር ተጠቃሚዎችን ያገለግላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮ ቴሌኮም ትልቅ ሥራ ሠርቷል ነው ያሉት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!