
ባሕር ዳር: ነሐሴ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ርዝስ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች ዘርፍ አስተባባሪና የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው እንደገለፁት የአጼ ፋሲል አብያተ መንግሥት ጥገና ሥራ አባቶችን ታሪካዊ አሻራ ጠብቆ ለትውለድ ከማስተላለፍ ባሻገር አንድነትና ወንድማማችነትን ለማጠናከር ፋይዳው ከፍተኛ ነው።
የአፄ ፋሲል አብያተ መንግሥትን ታሪካዊ ይዘቱና ቅርጽ ይዞ ታሪክን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ የጥገና ሥራው በጥሩ ደረጃ ላይ እየተከናወነ መኾኑን ገልጸዋል።
ጎንደር የአፍሪካ መናገሻና የንግድ ትስስርና የማኅበራዊ ግንኙነት ማዕከል ኾና ያገለገለችና የታሪክ ባለቤት ናት ያሉት አቶ ደሳለኝ የአሁኑ ትውልድ በመቻቻልና በመከባበር ባሕሉን በማዳበር ታሪክን ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ እንሚገባው ገልጸዋል ።
የአዘዞ -አርበኞች አደባባይ የአስፓልት መንገድ ሥራ ፕሮጀክት፣ የአፄ ፋሲል አብያተ መንግሥት የቅርስ ጥገኛ እና የፒያሳ የኮሪደር ልማት የሥራ እንቅስቃሴዎችን ያለበትን ደረጃ መመልከታቸውን ገልጸዋል።
በፌደራል መንግሥት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተነሳሽነት እየተሠሩ ያሉ ፕሮጀክቶች አሁን ላይ በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ነው የገለጹት ።
ጠቅላይ ሚኒስት ዐቢይ የአፄ ፋሲል አብያተ መንግሥትን ታሪካዊ ይዘቱና ቅርፅ ጠብቆ እንዲጠገን ማድረጋቸው ታሪክ የማይረሳው ሥራ መኾኑን ገልጸዋል ።
የኮሪደር ልማቱ የሥራ እድል በመፍጠር ፣የዕውቀት ሽግግርን መፍጠር እና ኢኮኖሚውን የሚያነቃቃ ከመኾኑ በላይ በሀገር ግንባታ የሚያበርክተው ሚና ከፍተኛ መኾኑን መመልከታቸውን ገልጸዋል ።
በአካባቢው መሥተዳድርና በኅብረተሰቡ ቅሬታ ሲያስነሱ የነበሩ የአዘዞ አርበኞች ዐደባባይ መንገድ ፕሮጀክት እና የመገጭ ግድብ ፕሮጀክት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከገመገሙ በኃላ ቀልጣፋና ፈጣን ምላሽ በመስጠት አሁን ላይ ግን በሰጡት አቅጣጫ መሰረት በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል ።
ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ ለወጣቱ የሥራ እድል ለመፍጠር የሰላም ዋጋ ከፍተኛ መኾኑን ገልጸዋል። ከጎርጎር ፕሮጀክት ጋር ተያይዞ በርካታ የሥራ እድሎች እንደሚፈጠሩ አቶ ደሳለኝ ተናግረዋል ።
የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ ኃላፊ ጋሻው አወቀ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ዳይሬክተር ዘውዱ ማለደ እና የከተማ አሥተዳደሩ መሪዎች በጉብኝቱ መገኘታቸቸን ከከተማ እሥተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!