“ዕድልና ፀጋን አሟጦ የተነተነ፣ ስጋቶችን የለየ እና ጥራት ያለው ዕቅድ ዝግጅት የራዕይ መዳረሻ ነው!” አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር )

24

ባሕር ዳር: ነሐሴ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር የከተማ፣ የክፍለ ከተማና የቀበሌ መሪዎች የሚሳተፉበት የ2016 የፓርቲና የመንግሥት ሥራዎች የ2016 ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዳል። የ2017 ዕቅድ ትውውቅ መድረክም በተሳካ ሁኔታ ማካሄዳቸውን በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተሞች ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) ገልጸዋል።

2016 በጀት ዓመት በችግር ውስጥ አልፈን ትላልቅ ግቦችን ማሳካት የቻልንበትና ሕዝባችንን የልማት አቅም ካደረግነው ፈተናዎችን ተሻግረን ብልፅግናችንን ማረጋገጥ እንደምንችል ትምህርት የተወሰደበትም ነው ብለዋል ዶክተር አሕመዲን።

በ2017 በጀት ዓመት ሁለንተናዊ ልማት ለመረጋገጥ የሚያስችሉ ስትራቴጂክ ግቦችን አቅደን ከከተማ እስከ ቀበሌ ካለው አመራር ጋር በቁጭትና እልህ ለመፈጸም ተገቢወን መግባባት አድርገናል ነው ያሉት።

ዶክተር አሕመዲን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልእክት በቀጣይ የሥራ ዘመን ስኬቶችን በማላቅና በማስፋት፣ ጥንካሬዎችን መለየት ይገባል ብለዋል።

የተለዩ ጉድለቶችን በመሙላት እና በማረም ከሕዝባችን ጋር በመኾን ደብረ ብርሃን ለኑሮ የምትመች እንዲሁም የለማች ከተማ ለማድረግ በየደረጀው የምገኝ አመራር ጠንክሮ መሥራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የፍትሕ ሥርዓቱን አገልግሎት አሰጣጥ ለማቀላጠፍ ተቋማቱን በቴክኖሎጂ ማጠናከር ይገባል” አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ
Next articleየቡሄ በዓል በኮምቦልቻ ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች ተከበረ።