“ከ39 ሺህ በላይ ማሳ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ሲስተም ውስጥ በማስገባት የመሬት ግብይት ተፈጽሟል” የደቡብ ወሎ ዞን መሬት መምሪያ

19

ደሴ: ነሐሴ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ወሎ ዞን መሬት መምሪያ ከወረዳ የዘርፉ መሪዎች ጋር የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የዕቅድ ትውውቅ መድረክ አካሂዷል። በበጀት ዓመቱ የተቋሙን ተልዕኮ የተረዳ ፈጻሚ ኀይል በመፍጠር እና በየደረጃው ዕቅዶችን በማዘጋጀት ወደ ተግባር በማስገባት በርካታ ሥራዎች የተሠሩበት ዓመት እንደነበር በሪፖርቱ ተመላክቷል። ተንታ፣ ወረኢሉ እና መቅደላ ወረዳዎች በበጀት ዓመቱ ከፍተኛ አፈጻጸም የነበራቸው ወረዳዎች መኾናቸውም ተገልጿል።

የመድረኩ ተሳታፊ የወረዳው መሬት ጽሕፈት ቤት ኀላፊዎች የበጀት ዓመቱ በሁሉም የሥራ ዘርፍ የተሻለ አፈጻጸም የነበረበት መኾኑን ገልጸዋል፡፡ ካለው የጸጥታ ችግር አኳያ በክልሉ በተሰጠው የቁጭት ዘመን ዕቅድ መሠረት ለ2017 ዓ.ም ከዚህ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ እንደሚሠሩም አስገንዝበዋል።

የደቡብ ወሎ ዞን መሬት መምሪያ ኀላፊ አብዱረህማን ይመር በ2016 በጀት ዓመት እንደ ክልል የተሰጠውን መመሪያ ተከትሎ በርካታ ተግባራትን ለማከናወን እንቅስቃሴ ሲደረግ ቆይቷል ብለዋል። ኀላፊው ከመሬት አሥተዳደር አኳያ ከ39 ሺህ 441 ሄክታር በላይ ማሳ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ሲስተም ውስጥ አስገብቶ ግብይት ተፈጽሟል ነው ያሉት።

ዘጋቢ:- ፊኒክስ ሀየሎም

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የብርሃን መውጫ፤ የምስጢር መገለጫ”
Next article“ፈተናውን በጽናት እና በማስተዋል የሚሻገር መሪ፤ ሀገርንም ሕዝብንም ማሻገር ይችላል” አቶ ደሳለኝ ጣሰው