“የጸና እና ቁርጠኛ መሪ በችግር ውስጥም ኾኖ ለውጥ ማምጣት ይችላል” አቶ ደሳለኝ ጣሰው

35

ጎንደር: ነሐሴ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አሥተዳደር የ2016 ዓ.ም የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2017 ዓ.ም የዕቅድ ትውውቅ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ መክፈቻ ላይ የተገኙት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ እና የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው የመንግሥት መሪዎች ክልሉ ከገባበት ችግር ለማውጣት ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

ኀላፊው የክልሉ መሪዎች በ2016 ዓ.ም የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ እና ልማት ለማስመዝገብ ጥረት አድርገዋል ብለዋል፡፡ ክልሉ በችግር ውስጥም ኾኖ የክልሉ መንግሥት ባለፉት ስድስት ወራት ትኩረት በመስጠት የ25 ዓመታት የልማት ዕቅድ አዘጋጅቶ ይፋ አድርጓል ነው ያሉት። ይፋ የተደረገውን ዕቅድ በየደረጃው ሁሉም እንደሚመክርበትም ነው አቶ ደሳለኝ ጣሰው ያስገነዘቡት፡፡
ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን የተውጣጡ መሪዎችም በዕቅዱ ዙሪያ እየመከሩ ነው።

ዘጋቢ፡- ተስፋዬ አይጠገብ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በቡሄ በዓል ጅራፍ የማጮህ ልምድ ምሳሌው መለኮታዊ ድምጹን ለማመላከት ነው” መላዕከ ገነት ቀሲስ ኃይሌ አየለ
Next article“በቀውስ ጊዜ አመራር የሕዝቡን ሰላም እና ደኅንነት ከማስጠበቅ ጎን ለጎን የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎች ተከናውነዋል” አሕመዲን መሐመድ (ዶ.ር)