“ክልሉ ካጋጠመው ቀውስ በፍጥነት ለመውጣት የቁጭት እቅድ አዘጋጅቷል” ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር)

37

ባሕር ዳር: ነሐሴ 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ ወሎ ዞን የ2016 በጀት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ መድረክ ተጠናቅቋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የተገኙት በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር) ባስላለፉት መልእክት “ክልሉ ካጋጠመው ቀውስ በፍጥነት ለመውጣት የቁጭት እቅድ አዘጋጅቷል” ብለዋል።

በየደረጃው እቅዱን መሠረት ያደረገ የፓርቲ እና የመንግሥት መዋቅሩ ውይይት በጋራ መግባባ ተጠናቅቋል ነው ያሉት። ለእቅድ አፈጻጸሙም የሥራ ስምሪት ምዕራፍ ላይ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች ተሠርተዋል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ዶክተር ዘሪሁን ፍቅሩ ባስተላለፉት መልእክት ለእቅዱ ተግባራዊነት ሁሉም አካል ኀላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል። በቀጣይም ክልሉ ያዘጋጀው እቅድ እስከ ሕዝቡ ድረስ ወረዶ ውይይት ከተደረገበት በኋላ የጋራ መግባባት ይፈጠርበታል ተብሏል።

የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም በየደረጃው ተገምግሞ ለቀጣይ በጀት ዓመት እቅድ ትግበራ መነሻ እርሾ የሚኾኑ ተሞክሮዎች ተቀምረውበታል ነው ያሉት ዶክተር ዘሪሁን።

እንደ ዞኑ ኮሙኒኬሽን መምሪያ መረጃ በተለይም የሕዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በተግባር ያረጋገጡ ስኬቶች በበጀት ዓመቱ እቅድ እንደ መነሻ ተካትተዋል ተብሏል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበክረምት በጎ ፈቃድ የማጠናከርያ ትምህርት በተጠናከረ መንገድ እየተሰጠ መኾኑን የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር አስታወቀ።
Next article“ከሰላም ሥራችን ጎን ለጎን ሕዝቡ አጥብቆ የሚሻውን የልማት ጥያቄ ለመመለስ በትኩረት እንሠራለን” የምዕራብ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳደር