
ባሕር ዳር: ነሐሴ 12/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ባስተላለፉት መልእክት ደኖች ለምድራችን ጤና እና ለሰው ልጅ ደኅንነት እጅግ አስፈላጊ ናቸው፤ ኦክሲጅንን ይሰጡናል፤ ካርቦንን ያከማቻሉ፤ አየር ንብረትን በመቆጣጠር የአየር ንብረት ለውጥን ተጽዕኖ ለመግራት ያገለግላሉ ብለዋል።
ደኖች በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ፍጥረታት መኖሪያ በመሆን የብዝኀ ሕይወት መገኛም ናቸው ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
“ያሉንን ደኖች እንጠብቅ። አዲስ ችግኞችን በመትከልም የደን ሽፋናችንን እንጨምር። ለነሐሴ 17 እንዘጋጅ!” ብለዋል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባጋሩት መልእክት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!