ከ556 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

40

ባሕር ዳር: ነሐሴ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በተያዘው የምርት ዘመን በመኽር እርሻ ከ556 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ አስታውቋል።

የመምሪያ ኀላፊ አበበ መኮንን በ2016/ 2017 የመኸር ምርት ዘመን ከ612 ሺህ ሄክታር በላይ ማሳ በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።

ኀላፊው ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስም 556 ሺህ 964 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን ገልጸዋል። አፈጻጸሙም 91 በመቶ እንደኾነ ነው የገለጹት።

የዞኑን ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሻሻሉ አሠራሮች ተግባራዊ እየተደረጉ ነው ብለዋል።

አቶ አበበ እስካሁን ድረስ በዘር ከተሸፈነው ማሳ ውስጥ 351ሺህ 409 ሄክታር ማሳ የተሻሻሉ አሠራሮችን በመጠቀም በዘር የተሸፈነ እንደኾነ ተናግረዋል።

በምሥራቅ ጎጃም ዞን በ2016/ 2017 ዓ.ም የመኸር ምርት ዘመን ከ23 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማምረት እየተሠራ መኾኑን ከዞኑ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከሩሲያ አምራቾች እና የዘርፉ ማኅበራት ጋር አብሮ መሥራት የሚያስችል ውይይት አካሄደ።
Next articleከ16ሺህ በላይ የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች የግብር ግዴታቸውን በወቅቱ መወጣታቸውን የምሥራቅ ጎጃም ዞን አስታወቀ።