ከአንድ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

17

ባሕር ዳር: ነሐሴ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 163 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።

በዛሬው እለት ወደ ሀገር የተመለሱት 947 ወንዶች፣ 200 ሴቶችና 16 ጨቅላ ህፃናት መኾናቸው ተገልጿል። ከተመላሾች መካከል 49 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የኽኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ ከ73 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለሳቸው የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበጎንደር ከተማ 61 መማሪያ ክፍሎችን እንደሚገነባ የአማራ ልማት ማኅበር ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ገለጸ።
Next articleገቢዎች ሚኒስቴር የጉምሩክ እና የታክስ አሥተዳደርን የሚዳስስ መጽሐፍ አስመረቀ፡፡