
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ሸዋ ዞን እና የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር የሰላም እና የፀጥታ ሥራዎች አፈፃፀም ተገምግሟል፡፡
በመድረኩ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተሞች እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አህመዲን መሀመድ (ዶ.ር)፣ የኮማንዶ እና አየር ወለድ እዝ ምክትል አዛዥ ብርጋዴል ጄኔራል አበባው ሰይድ፣ የደቡብ ዕዝ ኮር አዛዥ ብርጋዴል ጄኔራል ጌታቸው ሀብታሙ ተገኝተዋል፡፡
በመድረኩም አጠቃላይ የቀጣናው የሰላም ሁኔታ በዝርዝር ተገምግሞ የቀጣይ አቅጣጫም ተቀምጧል።
በአካባቢው የተሰማራው ጥምር ጦር ከአመራሩ እና ሕዝቡ ጋር በትብብር ጠንካራ ሥራ የተሠራ ስለመኾኑም ነው የተገለጸው፡፡
በቀጣይ አሁን ያለው አንጻራዊ ሰላም እና መረጋጋት ወደ ዘላቂ ሰላም እንዲሸጋገር የተጀመሩ ቀሪ ሥራዎችን በቀሪ ጊዜያት ማጠናቀቅ እንደሚገባም አቅጣጫ ተሰጥቷል።
በጋራ ግምገማ መድረኩ ይህ ሰላም እንዲመጣ መስዋዕትነት ለከፈሉ እና የበኩላቸውን ሚና ለተወጡ የፀጥታ መዋቅሩ እና ለአካባቢው ማኅበረሰብ ከፍተኛ መሪዎች ምሥጋና ማቅረባቸውን ከሰሜን ሽዋ ዞን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!