የኢትዮጵያ አየር መንገድ መግለጫ

80

ባሕር ዳር: ነሐሴ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ)እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ኦገስት 16/2024 ጠዋት ከሕንድ ሙምባይ ወደ አዲስ አበባ ለመብረር በዝግጅት ላይ ወደ ነበረ አውሮፕላን የሚጫኑ ሻንጣዎችን ይዞ ወደ አውሮፕላኑ በመጎተት ላይ በነበረ ጋሪ ላይ ከተጫኑ ሻንጣዎች በአንዱ እሳት ታይቷል።

ክስተቱ ጋሪው ከራምፕ አካባቢ ወደ አውሮፕላኑ በመሄድ ላይ ሳለ እንደተከሰተ ተስተውሏል።

ይህንንም ክስተት የተመለከቱ በሙምባይ ያሉ የደህንነት፣ የጸጥታ እና የእሳት አደጋ ባለሞያዎች እሳት የያዘውን ሻንጣ በመለየት እሳቱን በቁጥጥር ስር አውለዋል።

አውሮፕላኑ አስፈላጊው ተጨማሪ የደህንነት ፍተሻ ከተደረገለት በኋላ እና አስጊ ነገር አለመኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ በረራውን አካሂዷል።

የሙምባይ ኤርፖርት ባለስልጣናት እና የሚመለከታቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመግለጫው አካላት የክስተቱን ምንጭ በመመርመር ላይ በመኾናቸው ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን የምናሳውቅ ይኾናል ብሏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ የእናቶችን እና የሕጻናትን ሞት ለመቀነስ ያለመ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።
Next articleአምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ጋር ተወያዩ።