
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር የምክክር ተሳታፊዎች አጀንዳዎቻቸውን ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዛሬ በይፋ አስረክበዋል።
በኮሚሽኑ አስተባባሪነት በድሬዳዋ አሥተዳደር ከነሐሴ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ ዛሬ ተጠናቋል፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች አምባሳደር መሐሙድ ድሪር እና ኮሚሽነር ተገኘወርቅ ጌጡ (ዶ.ር) የድሬደዋ አሥተዳደር አጀንዳዎችን በይፋ መረከባቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!