
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በመላው ኢትዮጵያ የሲስተም ማሻሻያ ሥራ እያከናወነ በመሆኑ በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ የኃይል ጭነት በሚበዛባቸው ሰዓታት ዛሬና ነገ የኃይል መቋረጥ ሊያጋጥም እንደሚችል አሳውቋል።
የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ እንደገለጸው “ተቋሙ የማሻሻያ ሥራው አጠናቅቆ መደበኛ የኃይል አቅርቦት እስሰሚመለስ ድረስ፤ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንን ተገንዝባችሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉና ሌሎች ጊዜያዊ የኃይል አማራጮች እንድትጠቀሙ በአክብሮት እናሳውቃለን” ብሏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
