“በባሕር ዳር ከተማ ውስጥ የተፈጠረ የጸጥታ ችግር የለም” የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን

151

ባሕር ዳር: ነሐሴ 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሰላም አየር የሚኮሰኩሳቸው፣ ልማት እና የሕዝብ መረጋጋት እረፍት የሚነሳቸው፣ በወገን ሰላም ማጣትን ሀሴት የሚያደርጉ “በበሬ ወለደ” የውሸት ጋጋታ ጦር አውርድ ባይ የማኅበራዊ ሚዲያ አወናባጅ ሴረኞች አማካኝነት በክልላችን መዲና ባሕር ዳር ከተማ ችግር እንደተፈጠረ ለማስመሰል ሞክረዋል ሲል የአማራ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

“ይሁን እንጅ በከተማችን የተፈጠረ ምንም የጸጥታ ችግር የለም” ነው ያለው ኮሚሽኑ። ለዚህም የጸጥታ ኃይሉ በአስተማማኝ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲኾን ማኅበረሰቡ ተረጋግቶ የተለመደ መስተጋብሩን እንዲቀጥል እና ለጸጥታ ኃይሉ የተለመደ ትብብር እንዲያደርግ መልዕክት እናስተላልፋለን ሲል የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን በማኅበራዊ ትስስር ገጹ መልዕክት አስተላልፏል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የክልሉ የጸጥታ ኃይል ከፌዴራል የጸጥታ ኃይል ጋር በመኾን አካባቢውን ለመጠበቅ እና ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ በቂ ዝግጅት አለው” የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ
Next articleየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በመላው ኢትዮጵያ የሲስተም ማሻሻያ ሥራ እየተከናወነ መኾኑን ገለጸ።