“ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ልንሠራ ይገባል” ከንቲባ መንበሩ ዘውዴ

25

ባሕር ዳር: ነሐሴ 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም እና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ አካሂዷል።

በመድረኩ የከተማ ሥተዳደሩ ከንቲባ መንበሩ ዘውዴ በ2016 ዓ.ም የተከሰተው የሰላም እጦት በልማት እና በመልካም አሥተዳደር ሥራዎች ላይ ተፅዕኖ ቢያሳድርም የተለያዩ ተግባራትን መፈፀም ተችሏል ነው ያሉት።

“በ2017 በጀት ዓመት በችግሮች ላይ በማተኮር ዕቅድን ተግባራዊ ማድረግ እና ተጠያቂነትን ማስፈን በትኩረት የሚሠራበት ሊኾን ይገባል” ብለዋል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አብተው መኳንንት የ2016 በጀት ዓመት በርካታ ፈተናዎች የታለፈበት ነበር ብለዋል፡፡

ኀላፊው ዓመቱ የታቀዱ ሥራዎችን ወደ ተግባር ለመቀየር ጥረቶች ሲደረጉ የቆዩበት እንደኾነም ተናግረዋል፡፡

ከሰላም ማስከበር ሥራዎች ጎን ለጎን የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎችን ለመፈፀም ርብርብ መደረጉንም ተናግረዋል።

በቀጣይም በመሠረተ ልማት ግንባታ፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በኑሮ ውድነት ማቃለል እና በሌሎችም ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ሥራዎች ላይ ለመሥራት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል።

በዕቅድ ትውውቅ መድረኩ የተገኙ ተሳታፊዎችም በ2016 በጀት ዓመት በፈተና ውስጥ ኾነው ሢሠሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል፡፡ ወደ ፊትም የታቀዱ ሥራዎችን ለመፈፀም ዝግጁ መኾናቸውን ተናግረዋል።

በግምገማ እና በዕቅድ ትውውቅ መድረኩ የመምሪያ፣ የክፍለ ከተማ እና የቀበሌ መሪዎች ተሳትፈዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የመልካም አሥተዳደር ሥራዎችን እየሠራን ሰላምን ማስጠበቅም አንዱ ተግባር መኾን አለበት” አቶ ደሳለኝ ጣሰው
Next article“ጭር ሲል አልወድም ለማን ይበጃል?”