
ሰቆጣ: ነሐሴ 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሰቆጣ ከተማ “የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ መልዕክት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ ከአረንጓዴ አሻራ ጎን ለጎን የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ እና ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ እየተካሄደ ነው።
የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመተባበር የበጎ ፈቃድ ተግባራትን እያከናወነ ሲኾን በዚህም ከ3 ሺህ በላይ ችግኞች በትምህርት ተቋማት አካባቢዎች ተተክለዋል።
በመርሐ ግብሩም የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን፣ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ሥራ አሥፈጻሚዎች፣ የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር መሪዎች፣ የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የሰቆጣ ከተማ ወጣቶች እየተሳተፉ ነው።
ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!