የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከወሎ ዩኒቨርሲቲና በአካባቢው ከሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ጋር በመሆን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት እየሠራ መሆኑ ተገለጸ::

198

ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 02/2012 ዓ.ም (አብመድ) የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ከማል መሐመድ (ዶክተር) ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ግቢ፣ ከኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ከአማራ ብረታ ብረት ጋር በመሆን የፈጠራ ሥራዎችን እየሠሩ እንደሆነ አስታውቀዋል::

በእግር በመንካት የሚሠሩ የእጅ መታጠቢዎች፣ ለሕክምና ባለሙያዎች የሰውነት መሸፈኛ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ መሠራታቸውንም ዶክተር ከማል ገልጸዋል::

የአፍና አፍንጫ መሸፍኛው በኮምቦልቻ ጨርቃ ጨርቅ እና በተላጀ ጋርመንት ተሠርቶ ለማኅበረሰቡ የተሠራጨ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን ለሕክምና ባለሙያዎች የሚውለው የአካል መሸፈኛም ደረጃውን ጠብቆ መሠራቱ ታውቋል::

ዘጋቢ፡- አበሻ አንለይ

Previous articleከጦርነት እስከ ክትባት የዘለቀው የቅኝ ግዛት እሳቤ ውልድ፡፡
Next articleኩባንያው 700 ሺህ ብር የሚያወጡ የተለያዩ ግብዓቶችን ድጋፍ አደረገ፡፡