
ባሕር ዳር: ነሐሴ 10/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሠብሣቢ አስቻለ አላምሬ ምሥራቅ ጎጃም ዞን በደጀን ከተማ ባዘጋጀው ዞናዊ የአፈፃፀም ግምገማ እና የዕቅድ ትውውቅ መድረክ ላይ ተገኝተዋል፡፡
በመድረኩም ተገኝተው በክልሉ የተከሰተው የሰላም መደፍረስ በልማት እንቅስቃሴው ላይ ያሳደረው ጫና ከፍተኛ ቢኾንም በዞኑ የተከናወኑ የልማት ተግባራት አበረታች መኾናቸውን ተናግረዋል።
አቶ አስቻለ “በተያዘው በጀት ዓመት የታቀዱ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ግቦችን ለማሳካት በዞኑ በየደረጃው የሚገኙ መሪዎች ያሳዩት ተነሳሽነት እና ቁርጠኝነት ተስፋ ሰጭ ነው” ብለዋል።
የሕዝብ እንደራሴው የወከላቸው ሕዝብ የሚያነሳቸው የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎች እንዲፈቱ፣ የተጓተቱ እና በግጭት ምክንያት የቆሙ የልማት ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ እንዲገቡ በሕዝቡ የተሰጣቸውን አደራ ለመወጣት እየሠሩ መኾናቸውንም ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!