በሳዑዲ አረቢያ የሥራ ገበያ ፍላጎት እንዳለ እና ይህንን ታሳቢ ያደረገ ሥራ እየተሠራ እንደኾነ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

19

ባሕር ዳር: ነሐሴ 9/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ.ር) ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ በዘርፉ የተደረገውን ሪፎርም ተከትሎ የዜጎችን መብት፣ ደኅንነት እና ተጠቃሚነትን ባረጋገጠ መልኩ ሥምሪት ለማድረግ የተደረገው ጥረት ስኬቶች የተመዘገቡበት እንደነበር ተመላክቷል፡፡

በሳዑዲ አረቢያ የሥራ ገበያ ከፍተኛ የሰው ኀይል ፍላጎት እንዳለ የተገለጸ ሲኾን በዚህም የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለመውሰድ በሚያስችል መልኩ በቅንጅት እየተሠራ እንደሚገኝ ነው የተብራራው፡፡

በሳዑዲ ካለው ከፍተኛ የሰው ኀይል ፍላጎት አኳያ የሠለጠነ እና በከፊል የሠለጠነ የሰው ኀይል ስምሪት ላይ በልዩ ትኩረት እንደሚሠራም ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሂጅራ ባንክ የማኅበረሰቡን የፋይናንስ ፍላጎት እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሠራ መኾኑን ገለጸ።
Next articleሼህ መሐመድ አላሙዲን ለኢትዮጵያ ህዋ ሳይንስ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ዓለም አቀፉ አስትሮኖሚካል ኅብረት ዕውቅና ሰጣቸው።