
ባሕር ዳር: ነሐሴ 9/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ማስተካከያ ያላደረጉት ቀሪ ሁለት ትምህርት ቤቶች የሕግ አግባቡን ተከትሎ እንዲያስተካክሎ እንደሚደረግ ትምህርት መምሪያ ገልጿል።
የባሕር ዳር ከተማ ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ኃይለማርያም እሸቴ የግል ትምህርት ቤቶች የክፍያ አከፋፈል ራሱን የቻለ ሕግ እንዳለው ገልጸዋል። ይሁን እንጂ በከተማ አሥተዳደሩ የሚገኙ 28 ትምህርት ቤቶች በ2017 የትምህርት ዘመን ሕግን በጣሰ መንገድ የትምህርት ክፍያ ጭማሪ አድርገው እንደነበር ነው የገለጹት።
መምሪያው ከዚህ በፊት ትምህርት ቤቶች እንዲያስተካክሉ በደብዳቤ እና በመንግሥት ሚዲያ ከማሳወቅ ባለፈ ከተቋማቱ ተወካዮች ጋር በመወያየት እስከ ሐምሌ 19/2016 ዓ.ም እንዲያስተካክሉ አሳስቦም ነበር። በዚህም መሠረት ያለአግባብ ጭማሪ አድርገው ከነበሩ 28 የግል ትምህርት ቤቶች ውስጥ 26ቱ ማስተካከላቸውን ነው መምሪ ኀላፊው የገለጹት።
ማስተካከያ ያላደረጉት ሁለት ትምህርት ቤቶች የሕግ አግባቡን ተከትሎ እንዲያስተካክሎ እንደሚደረግ ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!