
ባሕር ዳር: ነሐሴ 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ክልላዊ የፖለቲካና አደረጃጀት ሥራዎች አፈጻጸም ግምገማ ተካሂዷል።
በግምገማ መድረኩ የ2017 በጀት ዓመት የቅድመ ዝግጅት ሥራ አፈጻጸም እና ባለፉት ሁለት ወራት የተከናወኑ የፖለቲካና አደረጃጀት ሥራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት መደረጉን ከአማራ ብልጽግና ፓርቲ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የአማራ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ በበጀት ዓመቱ ምርጥ ሥራዎቻችንን የበለጠ የሚያጠናክርና ክፍተቶቻችንን የሚያርም ሥራ በመሥራት የሕዝባችንን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይጠበቅብናል ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!