
ባሕር ዳር: ነሐሴ 8/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተሞች ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ እና የከተማ መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የምትገኘውን የአጣየ ከተማ ጎብኝተዋል።
ባለፉት ዓመታት በአካባቢው በተፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት ጉዳቶችን ያስተናገደችው የአጣየ ከተማ በቅርቡ ከመከላከያ ሠራዊት እና ከሕዝብ ጋር በተሠሩ ሥራዎች በከተማዋ አንጻራዊ ሰላም ስለመምጣቱም ተናግረዋል።
ዶክተር አሕመዲን ሙሐመድ ይኽ አንጻራዊ ሰላም እንዲሰፍን ዋጋ ለከፈሉ አካላት ከፍተኛ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልእክት “በአጣየ ከተማ የተጀመረው የሰላም ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁላችንም በጋራ እንድንሠራ ጥሪየን አቀርባለሁ” ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!