
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 29/2012 ዓ.ም (አብመድ) የዓለም ጤና ድርጅት የኮኖና ቫይረስ ክትባት በአፍሪካውን እንዲሞከር ከሰሞኑ ተመራማሪዎች ያቀረቡንት ሐሳብ አውግዟል፡፡
ሁለት የፈረንሳይ የሕክምና ሳይንስ ተመራማሪዎች የኮሮና ቫይረስ በአፍሪካውን ላይ እንዲሞከር ሐሳብ ማቅረባቸው አፍሪካውያንን አስቆጥቷል፡፡ በኋላም አንደኛው ዶክተር ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡
የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮና ወረርሽኝን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ላይ ጉዳዩን በተመለከተ ሐሳብ ሰጥተዋል፡፡ ዶክተር ቴዎድሮስ ይህንን ሐሳብ ያቀረቡት ተመራማሪዎችን ሐሳብ ‘‘ዘረኝነት ነው፤ አፍሪካ ቤተ ሙከራ አይደለችም’’ በማለት ሐሳባቸውን አውግዘዋል፡፡
ምንጭ፡- ሲጂቲኤን
በአስማማው በቀለ