
ደሴ: ነሐሴ 8/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በመርሐ ግብሩ ላይ የአማራ ክልል ሥራና ሥልጠና ቢሮ ኀላፊ ስቡህ ገበያውን (ዶ.ር) ጨምሮ የዞን እና የከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል። ተመርቀው ለአገልግሎት የበቁት የልማት ሥራዎች ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስለመኾናቸው የደሴ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ያሲን አመዴ ገልጸዋል።
21 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የተደረገበት የመንገድ እና የካናል ሥራ ተጠናቅቆ ዛሬ ወደ ሥራ መግባቱን ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል። የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን በዞኑ በተለያዩ አካባቢዎች ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መኾኑን ገልጸዋል።
መንግሥት ይህን ጅምር የልማት ሥራ አጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት አቶ አሊ ከሁሉም በላይ ሰላም ቀዳሚ ጉዳይ በመኾኑ ማኅበረሰቡ ለሰላም ዘብ መቆም ይገባዋል ነው ያሉት። ከመሠረተ ልማት ግንባታ ሥራዎች የምርቃት መርሐ ግብር ጎን ለጎን በከተማ አሥተዳደሩ አረንጓዴ አሻራን የማስቀመጥ መርሐ ግብር ተከናውኗል።
ዘጋቢ፡- ጀማል ይማም
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!