መድኃኒቶችን ከሕጋዊ ተቋማት መውሰድ እንደሚገባ የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሰበ።

18

ባሕር ዳር: ነሐሴ 8/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በኢንስቲትዩቱ የወባ ፕሮግራም ባለሙያ ይርዳው እምሩ እንዳሉት በክልሉ እየጨመረ የመጣውን የወባ በሽታ ከመከላከል ባለፈ ሕሙማንን የማከም ሥራ እየተሠራ ይገኛል። አሁን ላይ እየተስፋፋ የመጣውን የወባ በሽታ ለመከላከል ማኅበረሰቡ ሕጋዊ እውቅና ከተሰጣቸው የመንግሥት እና የግል የጤና ተቋማት ተመርምሮ መድኃኒቶችን በአግባቡ መውሰድ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተለይም ደግሞ “ቫይቫክስ” የተባለው የወባ በሽታ በጉበት ውስጥ ለዓመታት የመደበቅ እድሉ ከፍተኛ በመኾኑ ተገቢውን ክትትል ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል። በባለሙያ የታዘዘን መድኃኒት በአግባቡ ሙሉ በሙሉ ያለመውሰድ ችግር መኖሩን ያነሱት ባለሙያው ይህ ደግሞ በሽታው ዳግም እንዲያንሰራራ እና የመድኃኒት መላመድን እንዲከሰት እንደሚያደርግ ነው የገለጹት። የመድኃኒት መላመድ ሰዎችን ለተጨማሪ ምርመራዎች በመዳረግ ለተጨማሪ ወጭ ያጋልጣል።

ችግሩን ለመቅረፍ የታዘዘውን መድኃኒት በተቀመጠው ጊዜ መውሰድ፣ ከመድኃኒቱ ጋር አብረው ከማይሄዱ ነገሮች መታቀብ፣ በኮንትሮባንድ የሚገቡ እና ጥራታቸውን ያልጠበቁ መድኃኒቶችን ከመውሰድ መቆጠብ እንደሚገባ የገለጹት ባለሙያው ከሕጋዊ ተቋማት ተመርምሮ መድኃኒት መውሰድ ይገባል ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከሥራ ውጭ ህልማችንን የምንፈታበት ሌላ መንገድ ስለሌለን የፖለቲካ ዕሳቤያችን ሥራ ብቻ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር)
Next article“ኀብረተሰቡ በተደጋጋሚ የሚያነሳቸውን የመልማት እና በተገቢው መንገድ የመገልገል መብቱን ልናረጋግጥ ይገባል” ኢብራሂም መሐመድ (ዶ.ር)