“ከሥራ ውጭ ህልማችንን የምንፈታበት ሌላ መንገድ ስለሌለን የፖለቲካ ዕሳቤያችን ሥራ ብቻ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር)

20

ባሕር ዳር: ነሐሴ 8/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በ35 ሄክታር መሬት ላይ ከቻይናው “ሲሲሲሲ” ጋር በአጋርነት የሚገነባው የአዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በከተማ ውስጥ አዲስ ከተማን የመገንባት ያህል ግዙፍ ፕሮጀክት ነው ተብሏል፡፡ ፕሮጀክቱ በውስጡ ትላልቅ ሞሎችን፣ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን፣ ቢሮዎችን፣ የትምህርት ተቋማትን፣ የጤና ተቋማትን እንዲሁም ሰፋፊ የመዝናኛ እና የውኃ አካላትን፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላትን ያካተተ መኾኑ ተመላክቷል።

ይህ የአዲስ ቱሞሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለከተማዋ አዲስ ገጽታ የሚያላብስ፣ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን የሚያጎላ፣ ተጨማሪ የውበት ምንጭ የሚኾን ስለመኾኑ ነው የተገለጸው፡፡ ፕሮጀክቱ ለነዋሪዎች ሰፊ የሥራ ዕድል የሚፈጥር፣ ንግድን የሚያሳልጥ፣ ትልቅ ዓለም አቀፍ የግብይት ማዕከል እንደሚኾንም ተጠቅሷል።

ማኅበራዊ አገልግሎቶች የሚሰጡ መሠረተ ልማቶችን ያካተተ መኾኑን እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቆ ወደ ሥራ እንደሚገባም ነው የተገለጸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር) በማኅበራዊ ትሥስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት “ከሥራ ውጭ ህልማችንን የምንፈታበት ሌላ መንገድ ስለሌለ ያለን የፖለቲካ ዕሳቤ ሥራ ብቻ ነው፤ በዚህ መንገድ የመዲናችንን የነገ መልክ የሚያሳየውን የ’አዲስ ቱሞሮ’ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታን ዛሬ አስጀምረናል” ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት የአዲስ ቱመሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ ተጀመረ።
Next articleመድኃኒቶችን ከሕጋዊ ተቋማት መውሰድ እንደሚገባ የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሳሰበ።