የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማኅበር የዘንድሮ ማዳበሪያ ማጓጓዝ ሥራ ማጠናቀቁን አስታወቀ።

10

ባሕር ዳር: ነሐሴ 8/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማኅበር የ2016 ዓ.ም የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዝ ሥራውን በተሳካ ሁኔታ ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡ 266 ሺህ 770 ሜትሪክ ቶን ማዳበሪያ በ103 ባቡሮች በማጓጓዝ ከዚህ ቀደም ከተመዘገበው ሁሉ የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ገልጿል።

አክሲዮን ማኅበሩ ለዚህ ስኬት አስተዋጽዖ ላበረከቱ አጋር አካላት ምስጋና አቅርቧል። ለቀጣዩ ዓመትም አፈጻጸሙን ይበልጥ ለማሳደግ እንደሚሰራም ነው የጠቆመው፡፡ በቀጣይም ከዚህ ቀደም ከነበረው የገበያ ድርሻ 14 በመቶ ወደ 20 በመቶ ወይም ከዚያ በላይ የማሳደግ ዕቅድ እንዳለው ከኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማኅበር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article6 ነጥብ 9 ሚሊየን ተማሪዎችን ለመመዝገብ ማቀዱን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት የአዲስ ቱመሮ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ግንባታ ተጀመረ።