
ባሕር ዳር: ነሐሴ 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ ኢትዮጵያ የምታስተናግደውን ሀገር አቀፍ የግብርና ኢንቨስትመንት ፎረም እና አውደ ርዕይን አስጀምረዋል፡፡
ፎረሙ በትብብር የመሥራት አድማሳችንን ለማስፋት እና በግብርናው ዘርፍ ያለንን ፀጋ አውጥተን እንድንጠቀም በእጅጉ ይረዳናል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። “የግብርናችንን እምቅ አቅም እና ጸጋ እንጠቀም” ሲሉም በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ መልእክታቸውን አስፍረዋል።
ፎረሙ በሚኖረው የሁለት ቀናት ቆይታ ምርት እና አገልግሎትን እንዲሁም ዘመን ያፈራቸውን ቴክኖሎጂዎች ለማስተዋወቅና ባለሀብቶች በዘርፉ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!