የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ የአፈር ለምነትን ለመጨመር ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መኾኑን ገለጸ፡፡

8

ደብረ ብርሃን: ነሐሴ 7/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምርታማነትን ለማሳደግ የአፈር ለምነት ላይ መሥራት አበርክቶው የጎላ ስለመኾኑ ይነገራል፡፡ ይኽንን ተግባር የተሳካ ለማድረግ በደብረ ብርሃን ከተማ የአፈር ለምነት ማሻሻያ የንቅናቄ ተካሂዷል፡፡ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ኅላፊ መርሻ አይሳነው እንዳሉት ምርት እና ምርታማነትን ለማሻሻል የአፈር ለምነት ላይ መስራት ያስፈልጋል፡፡

ለዚህ ደግሞ እርጥበትን የምናገኝበት የክረምት ወራት ላይ ስለምንገኝ የተፈጥሮ ማዳበሪያ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሠራት አለበት ብለዋል፡፡ የደብረ ብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ ወርቃለማሁ ኮስትሬ በበኩላቸው አርሶ አደሩ የዘመኑ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ምርትን የማሳደግ ባሕሉን ሊያዳብር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ የግብርና ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት ርብርብ ያስፈልጋል ነው የተባለው፡፡ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች የአፈር ለምነትን በማሻሻል የምርት ጭማሬ እንዲኖር በአስተዳደሩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራበት ይገኛል ተብሏል፡፡

ዘጋቢ፦ ፋንታነሽ መሃመድ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሃይማኖታዊ እና ባሕላዊ በዓላትን ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየሠራ መኾኑን የአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡
Next articleየማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲው በተሳካ ሁኔታ እንዲተገበር የፍትሕ እና የፀጥታ ተቋማት ሚና የላቀ መኾኑ ተጠቆመ።