
ባሕር ዳር: ነሐሴ 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “ወጣቶችን በቴክኖሎጂ ማብቃት ለዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት” በሚል መሪ መልዕክት ዓለም አቀፉ የወጣቶች ቀን እየተከበረ ነው።
በዓለም ለ24ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ለ21ኛ ጊዜ የዓለም ወጣቶች ቀን ሲከበር ወጣቶች ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ችግር ፈቺ የፈጠራ ሥራዎችን በመሥራት ማኅበረሰባቸውን እንዲያገለግሉ ታሳቢ ያደረገ መኾኑን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ.ር) ገልጸዋል።
ሚኒስትሯ ወጣቶች ሥራ ጠባቂ ሳይኾኑ ሥራ ፈጣሪ እንዲኾኑ ማበረታታት እና አጋዥ ፖሊሲዎችን መቅረጽ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።
በበዓሉ ላይ የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ የልማት ድርጅቶች ተወካዩች፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የክልል እና የከተማ አሥተዳደሩ ወጣት አደረጃጀት መሪዎች እና ወጣቶች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡- ቤተልሄም ሰለሞን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!