
አዲስ አበባ: ነሐሴ 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የግብርና ሚኒስቴር ከነሐሴ 8 እስከ ነሐሴ 9 /2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄደውን ሀገራዊ የግብርና ኢንቨስትመንት ፎረምን በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የፎረሙና የኤግዚቢሽኑ ዋና ዓላማ በግብርናው ዘርፍ ያለውን አቅም ለማሳደግና ልምድ ለመለዋወጥ መኾኑን መግለጫውን የሰጡት የግብርና ሚኒስቴር ዴኤታ ሶፊያ ካሳ (ዶ.ር) ገልጸዋል። በውይይቱ ግብርናውን ማዘመን የሚችሉ የልምድ ልውውጦች እንደሚካሄዱ እና ባለሀብቶች ምርቶቻቸውን እንደሚያስተዋውቁ ዶክተር ሶፊያ ገልጸዋል።
በፎረሙ ከክልሎች የተውጣጡ አርሶ አደሮች ተሳታፊ እንደሚኾኑና ከ6 መቶ በላይ ከውጭ የተመዘገቡ ተሳታፊዎች እንደሚገኙ በመግለጫው ጠቅሰዋል፡፡ ከነሐሴ 8 እስከ 9 በሚሊኒየም አዳራሽ ፎረሙና ኤግዚቢሽኑ ክፍት ስለሚኾኑ ሁሉም ተገኝቶ የሀገሪቱ ግብርና የት እንደደረሰ መጎብኘትና አስተያየቱን መስጠት እንደሚችልም በመግለጫው ተመላክቷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!