“አብሮነት እና ወንድማማችነት ብቸኛ መውጫ በራችን ነው፤ ያለአብሮነት ሀገር ማሻገር አይቻልም” የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አሕመድ አሊ

6

ባሕር ዳር: ነሐሴ 6/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና የአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ አዋሳኝ ቀበሌዎች ከአካባቢው የተለያዩ የማኅበረሰብብ ክፍሎች ጋር የግጭት መፍቻ የእርቀ ሰላም መርሐ ግብር አካሂደዋል። የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አሕመድ አሊ ሁለት ሕዝቦች የሚል ታሪክ አክትሞ አንድ ሕዝብ ኾነን ሀገር በጋራ እናሻግራለን ሲሉ ተናግረዋል።

ዋና አስተዳዳሪው “አብሮነት እና ወንድማማችነት ብቸኛ መውጫ በራችን ነው፤ ያለአብሮነት ሀገር ማሻገር አይቻልም” ነው ያሉት። የኦሮሞ ሕዝብ የኔ ሕዝብ ነው የሚል የአንፆኪያ ሕዝብ፣ የአማራ ሕዝብ የኔ ሕዝብ ነው የሚል የኦሮሞ ሕዝብ እንዲፈጠር አበክረን እንሠራለን ሲሉ ተናግረዋል።
ከፋፋይ የግለሰብ ፍላጎቶችን በመተው አብሮነትን፣ ሰላምን እና ልማትን በጋራ እንዘራለን ብለዋል።

የአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አማከል ደምሴ እንደተናገሩት ወንድማማች ሕዝቦች እየተጋጩ እና እየተገፋፉ መኖር የለባቸውም ብለዋል። የአብሮነት እሴቶችን ማስቀጠል ይገባል፤ ቋንቋ መግባቢያ እንጅ መለያያ ሊኾን አይገባም ብለዋል። የ102ኛ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ኮሌኔል ሰለሞን ፀጋየ እንደገለጹት የሰሜን ሸዋ እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አብሮ የኖረ ሕዝብ ነው አሁንም አብሮ ይኖራል። የሃይማኖት አባቶች ለእውነት እና ለሰላም መሥራት አለባችሁ ብለዋል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን መምሪያ ማኀበራዊ ትስስር ገጽ እንደሚያመለክተው ኮሌኔል ሰለሞን ፀጋየ ቀጣናው ሰላም እንዲኾን ከሠራን ለሀገር የሚተርፍ ፀጋዎች አሉን ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል በጎንደር ከተማ ዳግም የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን እየተመለከቱ ነው፡፡
Next articleየመገጭ ግድብን በተያዘለት የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ እየተሠራ መኾኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ።