
ባሕር ዳር: ነሐሴ 6/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በሰጡት የሥራ አመራር በጎንደር ከተማ ዳግም የተጀመሩ የልማት ፕሮጀክቶችን የሥራ እንቅስቃሴ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እየተመለከቱ ነው፡፡
አሁን ላይ የመገጭ የመስኖ እና የመጠጥ ውኃ ግድብ ፕሮጀክት የሥራ እንቅሰቃሴን እየተመለከቱ ያሉት ሚኒስትሩ የአዘዞ ጎንደር የኮንክሪት አስፓልት መንገድ ሥራ እንቅስቃሴን እንደሚመለከቱም ይጠበቃል፡፡
እንደ ኢዜአ ዘገባ በከተማው የተጀመረውን የኮሪደር ልማት እና ዓለም አቀፍ ቅርስ የኾነውን የአጼ ፋሲል አብያተ መንግሥት የቅርስ ጥገና ሥራንም ከተመለከቱ በኋላ ሥለ ሥራው ሃሳባቸውን እንደሚያጋሩም ነው የተገለጸው፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!