የድህረ ምረቃ ፕሮግራም መግቢያ ፈተና እስከ ነሐሴ 10 ድረስ መራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

13

ባሕር ዳር: ነሐሴ 6/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ትምህርት ሚኒስቴር የድህረ ምረቃ ትምህርት ለመማር ወጥ የመግቢያ ፈተና እንደ ሀገር አቀፍ መስጠት መጀመሩ ይታወሳል፡፡

የ2017 ዓ.ም የመግቢያ ፈተናውን ለመስጠት ተማሪዎችን ለመመዝገብ ከሐምሌ 24 እስከ ነሐሴ 5/2016 ዓ.ም ድረስ አቅዶ ነበር። ሚኒስቴሩ ዛሬ ማለዳ ባወጣው መረጃ ደግሞ ምዝገባው ለተከታታይ አምስት ተጨማሪ ቀናት ተራዝሟል፡፡

ፈተናውን መውሰድ የሚፈልጉ የድህረ ምረቃ ተፈታኞች እስከ ተጠቀሰው ቀን በትምህርት ሚኒስቴር የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ላይ በተቀመጠው ሊክ አማካኝነት መመዝገብ ይችላሉ ሲልም አሳስቧል፡፡

በግልም ኾነ በመንግሥት የሁለተኛ ዲግሪ ወይም ሦስተኛ ዲግሪ መማር የሚፈልጉ አመልካቾች ቅድሚያ ይህንን ፈተና ማለፍ ይጠበቅባቸዋል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ለሥራ ጉብኝት ጎንደር ከተማ ገቡ።
Next articleበዞኑ ከሚገኙ ግብር ከፋዮች ውስጥ 85 በመቶ የሚኾኑት ከፍለው ማጠናቀቃቸውን የደቡብ ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ ገለጸ።