
ባሕር ዳር: ነሐሴ 6/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል ለሥራ ጉብኝት ዛሬ ጠዋት ላይ ጎንደር ከተማ ገብተዋል
ሚኒስትሩ ወደ ጎንደር ከተማ ሲገቡ የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ ደብሬ የኋላን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በአጼ ቴዎድሮስ አየር ማረፊያ አቀባበል ተደርጓላቸዋል።
ሚኒስትሩ በፌደራል መንግሥት እየተከናወኑ ያሉ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ይመለከታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!