1 ሺህ 209 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

23

ባሕር ዳር: ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 209 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ወደ ሀገር የተመለሱት ዜጎች 1ሺህ 34 ወንዶች፣ 154 ሴቶች እና 21 ጨቅላ ሕፃናት ሲኾኑ ከእነዚህ መካከል 18 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የኾኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ሥራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ከሚያዚያ 04/2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ ከ71ሺህ 700 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ጠቁሟል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleምሥጋና
Next articleበኮምቦልቻ ከተማ ያለበቂ ምክንያት በተለያዩ እቃዎች ላይ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ ላይ የተወሰደው እርምጃ ተገቢ መኾኑን ነዋሪዎች ገለጹ።