
🙏ዛሬ የምናመሠግናቸው ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬን ነው
🙏ዶክተር ወልደመስቀል ኮስትሬ (1939 – 2008 ዓ.ም)
🙏 እ.አ.አ 1972 በጀርመን የሙኒክ ኦሎምፒክ ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ለነበሩት ንጉሤ ሮባ ምክትል አሠልጣኝ በመኾን ነበር ወደ አሠልጣኝነቱ ዓለም የገቡት
🙏በስፖርት ኮሚሽን በከፍተኛ ባለሞያነትም ሠርተዋል
🙏ከ1992 ባርሴሎና እስከ 2008 ቤጂንግ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ኾነው አገልግለዋል
🙏ኢትዮጵያ በዓለም አደባባይ ስሟ ከፍ ብሎ እንዲጠራ ያደረጉትን የ5 ሺህ እና የ10 ሺህ ሜትር ባለድል አትሌቶች አፍርተዋል
🙏አሠልጣኝ ኾነው በተሳተፉባቸው አምስት የኦሎምፒክ ውድድሮች ለኢትዮጵያ 13 የወርቅ 5 የብር እና 10 የነሐስ በድምሩ 28 ሜዳሊያዎችን ማስገኘታቸው ተመዝግቦላቸዋል
🙏በ2006 ዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የዓመቱ ምርጥ አሠልጣኝ ብሎ ሸልሟቸዋል
🙏በስፖርት የ2007 ዓ.ም የበጎ ሠው ሽልማት አግኝተዋል