ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ተወያዩ።

27

ባሕር ዳር: ነሐሴ 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን ነሐሴ 4 ቀን 2016 ዓ.ም የስልክ ውይይት አድርገዋል። የሁለቱ መሪዎች ውይይት በሁለትዮሽ ጉዳዮች በተለይም የንግድ መጠንን በእጥፍ በማሳደግ ላይ ያተኮረ ነበር። ቀጣናዊ ትብብር ማጠናከርን በተመለከተም ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፕሬዝዳንት ጣይብ ኤርዶዋን በኢትዮዽያ እና በሶማሊያ መካከል የተከሰተውን የሃሳብ ልዩነት ለመፍታት ላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል። የ120 ሚሊዮን ሕዝብ ሀገር ለኾነችው ኢትዮጵያ በጋራ ስምምነት መንገድ የባሕር በር የማግኘት አስፈላጊነትንም አጽንኦት ሰጥተው እንደተወያዩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለውጥን ለምን እንፈራለን?
Next article“የተከዜን ጎርፍ ከላይ ወደታች እያየን ለመራመድ በመብቃታችን ተደስተናል” የዝቋላ እና ስሃላ ሰየምት ወረዳ ነዋሪዎች