“ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደ ትናንቱ ሁሉ ዛሬም በጀግኖች ልጆቿ የከበረ ተጋድሎ ስሟ በዓለም መድረክ ከፍ ብሎ መታየቱ ነገም ይቀጥላል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

43

ባሕር ዳር: ነሐሴ 4/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በ33ኛው የፓሪስ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ መዳሊያ በወንዶች ማራቶን አሳክታለች።

የተገኘውን ድል ተከትሎ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ርእሰ መሥተዳድሩ በመልዕክታቸው በፓሪስ ኦሎምፒክ በተካሄደው የወንዶች ማራቶን ውድድር ለሀገራችን ክብር፤ ለመላው ሕዝባችን ወደር የለሽ ደስታ ያጎናጸፈን ጀግናው አትሌት ታምራት ቶላ ባስመዘገበው ድል እጅግ ላቅ ያለ ደስታ ተሰምቶኛል ነው ያሉት።

“ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደ ትናንቱ ሁሉ ዛሬም በጀግኖች ልጆቿ የከበረ ተጋድሎ ስሟ በዓለም መድረክ ከፍ ብሎ መታየቱ ነገም ይቀጥላል” ብለዋል።

እንኳን ደስ ያላችሁ፤ እንኳን ደስ ያለን!

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleኢትዮ ቴሌኮም ዲጂታል ኢትዮጵያን የመፍጠር እሳቤውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ።
Next article👉የቱሪዝም አባት